በአሜሪካን ሃገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ህብረት አስተባባሪነት በሳኡዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መበቃወም በዋሽንግተን የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰልፍ ወጡ፡፡
ሰልፈኞቹ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች መካከል ‘በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ይቁም’፣ ‘ሕጻናትና ሴቶች ጥበቃን እንጂ የመብት ጥሰትን አይፈልጉም’ እንዲሁም ‘ኢትዮጵያውያን ይህ አይገባቸውም’ የሚሉ ይገኙባቸዋል፡፡