በጀርመን የሚኖሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ማህበረሰብ አባላት ‘ሰላምና መረጋጋት ለምስራቅ አፍሪካ’ በሚል ርዕስ በፍርንክፈርት ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

ሰልፉን በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ  ከኤርትራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፣ በወቅቱ ሰልፈኞቹ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ካስተጋቧቸው መልዕክቶች መካከል ‘በውስጥ ጉዳያችን ወሳኝ አንፈልግም’፣ ‘ኢትዮጵያ ሉአላዊ ሀገር ነች!’፣ ‘የዓለም መሪዎች የህወሓትን የጦር ወንጀል ሊያወግዙት ይገባል!’፣ ‘ሕወሃት አሸባሪ ድርጅት ነው!’፣ ‘የመከላከያ ሠራዊት የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስከበር የሚያደርገውን ፍልሚያ እንደግፋለን!’ እንዲሁም ‘ክብር ለጀግኖቻችን!’ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡