ዳያስፖራው በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ ላደረገው አስተዋጽኦ የአማራ ክልላዊ መንግስት የዕውቅና ማስታወሻ ሰጠ።
ክልሉ ‘በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው የተከፈለ መስዋዕትነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት’ በሚል መሪ መዕልክት በባህር ዳር ከተማ ባካሄደው የእውቅና እና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ነው ማስታወሻው የተበረከተው።
በትላንትናው ዕለት በተካሄደው የእውቅና እና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች መገኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ለህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ክልሉ ለዳያስፖራው አስተዋጽኦ ስለሰጠው ዕውቅና እያመሰገነ፣ በቀጣይም የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚሰራ ይገልጻል።