1. የፍራንኮ ቫሉታ የድጋፍ ደብዳቤ ለማፃፍ መሟላት ያለባቸው፡-
 2. በኤጀንሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ …………….. 1 ኮፒ
 3. የታደሰ የኢንቨስትመንት ፍቃድ / የንግድ ፈቃድ………….1 ኮፒ
 4. ለስራው ቦታ ከመንግስት መረከባቸውን ወይም ተከራይተው ስራውን እየሰሩ መሆኑን የሚያሳይ ሰነድ……………..1 ኮፒ
 5. ዜግነት ካልቀየሩ የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት 1 ኮፒ እና የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የመኖሪያ ፈቃድ /Residence ID…….1 ኮፒ
 6. ዜግነት ከቀየሩ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ…………………1 ኮፒ
 7. የኢንቨስትመንቱ/የንግድ ፍቃዱ በማህበር /በPLC/ ከሆነ ጥያቄውን ያቀረበው ዳያስፖራ የPLCአባል መሆኑን ለማረጋገጥ የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብና የመመስረቻ ጽሑፍ አቅርበው ማሳየት አለባቸው

 ማስታወሻ ፡-

 • ጥያቄው በተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድና የቀበሌ መታወቂያ ከዋናው/ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር ሲያቀርቡ ፈቃዱን ለሰጠው ተቋም ወይም ለኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል ።

 2. በኢንቨስትመንት/በንግድ ለመሳተፍ የድጋፍ ደብዳቤ ለማፃፍ መሟላት ያለባቸው ፡-

 1. በኤጀንሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ …………….. 1 ኮፒ
 2. ዜግነት ካልቀየሩ የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት 1 ኮፒ እና የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የመኖሪያ ፈቃድ /Residence ID…….1 ኮፒ
 3. ዜግነት ከቀየሩ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ…………………1 ኮፒ
 4. የኢንቨስትመንቱ/የንግድ ተሳትፎ ፍላጎቱ በማህበር /በPLC/ ከሆነ ጥያቄውን ያቀረበው ዳያስፖራ የPLCአባል መሆኑን ለማረጋገጥ የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብና የመመስረቻ ጽሑፍ አቅርበው ማሳየት አለባቸው

 ማስታወሻ  

 • ጥያቄው በተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድና የቀበሌ መታወቂያ ከዋናው/ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር ሲያቀርቡ ለሚፈልጉት ክልል/ከተማ አስተዳደር የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል ።

 3.የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን (TIN) ለማግኘትና የድጋፍ ደብዳቤ ለማፃፍ መሟላት ያለባቸው፡-

 በኤጀንሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ …………….. 1 ኮፒ

 • የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ዜግነት ከቀየሩ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ…………………1 ኮፒ
 • የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የመኖሪያ ፈቃድ /Residence ID…….1 ኮፒ
 • ከኢትዮጵያ ሚስዮን (ኤምባሲ፡ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት) የተላከ ደብዳቤና በወረቀት የተሰጠ የጣት አሻራ ሰነድ

ማስታወሻ ፡-

ጥያቄው በተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማረጋገጫ ሰነድና የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ ከዋናው/ኦሪጂናል ዶክመንት ጋር ሲያቀርቡ ለኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል።

4.የውጭ ምንዛሪ አካውንት (Diaspora Account) ለመክፈትና የድጋፍ ደብዳቤ ለማፃፍ መሟላት ያለባቸው ፡-

 1. በኤጀንሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ ……….. 1 ኮፒ
 2. የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም ዜግነት ከቀየሩ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ዜጋ መታወቂያ…………………1 ኮፒ
 3. ዳያስፖራው በውጭ ሃገር ከአንድ አመት በላይ የቆየ መሆኑን የሚያሳይ በቂ ማስረጃ
 • በሚኖርበት ሃገር ከሚገኘው የኢትዮጲያ ሚሲዮን (ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ) ከአንድ ዓመት በላይ መኖሩን የሚያሳይ ደብዳቤ ወይም የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የመኖሪያ ፈቃድ /Residence ID/ …… 1 ኮፒ ሲያቀርብ ለሚፈልገው ባንክ የውጭ ምንዛሬ አካውንት እንዲከፍት የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፋል።

ማስታዎሻ

 • የዳያስፖራ ተቀማጭ ሂሳብ የመኖሪያ ቤት መግዣ/መስሪያ የቁጠባ ሂሳብ (Diaspora Mortgage saving account) በስተቀር በውክልና መክፈት አይቻልም።
 • የውጭ ምንዛሬ አካውንት መክፈት የሚቻለው በአሜሪካን ዶላር, በእንግሊዝ ፓውንድ እና ዩሮ ብቻ ነው፡፡
 • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ( መመሪያ ቁጥር FXD/64/2019) መሰረት ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች/ ለምሳሌ ሪያድ፣ጅዳ፣ኳታር/ዶሀ/፣የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት/ ዱባይና አቡዳቢ/፣ኩየት፣ኦማን ፣እስራኤል፣ቤሩት/ እና ከጎረቤት ሀገራት/ ለምሳሌ ሱዳን ፣ጅቡቲ፣ኬንያ፣ኤርትራ፣ሶማሌ ላንድ/ የሚመጡ የዳያስፖራ ባለጉዳዮች የውጭ ምንዛሬ አካውንት መክፈት የሚችሉት በሚኖሩበት ሀገር ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮን (ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት) ከአንድ አመት በላይ ነዋሪ መሆናቸውን እና የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን/ Residence ID/ ያረጋገጠበትን የሚያሳይ ሰነድ / መረጃ ሲያመጡ የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፍላቸዋል ፡፡

5.የ40/60 የቤቶች ልማት ፕሮግራም በተመለከተ የቁጠባ ክፍያን ከዶላር ወደ ብር ለመቀየር እና የድጋፍ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማፃፍ መሟላት ያለባቸው፡-

 1. በኤጀንሲው የተዘጋጀውን የማመልከቻ ቅጽ ……….. 1 ኮፒ
 2. የአገልግሎት ዘመኑ ያላለቀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም በሊሴፓሴ የጉዞ ሰነድ ወደ አገራቸው የገቡ ….1 ኮፒ (የፓስፖርቱ ወይም የሊሴፓሴው ኮፒ)
 3. በኢትዮጵያ ፓስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ጠቅልለው ከተመለሱ አንድ አመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው (ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ኤርፖርት ውስጥ በኢሚግሬሽን ፓስፖርቱ ላይ ማህተም የተመታበትን ቀን በማየት ጊዜውን በማወቅ) ………..1 ኮፒ
 4. የቆጠቡበትን የሚያሳይ የባንክ ደብተር የፊት ለፊት ገፅ…………1 ኮፒ

ማስታወሻ

 • ከኖሩበት አገር የኢትዮጲያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ጠቅልለው መመለሳቸውን ጠቅሶ የቤት መገልገያ እቃ/ መኪና እንዲያስገቡ ለጉምሩክ ኮሚሽን የተጻፈላቸውን ደብዳቤ የያዙ ወይም በሊሴ ፓሴ የጉዞ ሰነድ ወደ አገር የገቡትና የመኖሪያ ፈቃድ የተሰረዘባቸው ዜጎች አንድ አመት እንዲቆዩ አይጠበቅባቸውም፡፡
 • ባለጉዳዩ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እያንዳንዱን 1 ቅጂ/ኮፒ ከኦሪጂናል ዶክመንት ጋር ሲያቀርብ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድጋፍ ደብዳቤ ይጻፍለታል።